የኢትዮጵያ የውሃና የኢነርጂ ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

የFBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ምስል

የኢትዮጵያ የውሃና የኢነርጂ ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ሳምንቱ “የውሃና ኢነርጂ ዘርፎች ሽግግር ለአዲሲቷ የተስፋ አድማስ” በሚል መሪ ቃል በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት የሚቆየው ሳምንት በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚካሄድ ይሆናል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፥ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት እድገት የታዳሽ ሀይል ልማት ዘርፍ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ይህም ኢትዮጵያ በ2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፈ እያደረገች ያለችውን ጥረት ለማሳካት ያግዛል ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም ግብርናን በማዘመንና ምርታማነትን በማሳደግና የሽያጭ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ለሀገሪቱ እድገት ብሎም የዜጎች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አንስተዋል።

የውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ያላትን የውሃ ሃብት በአግባቡ እየተጠቀመችብት አለመሆኑን አብራርተዋል።

ሀገሪቱ ያላትን የውሃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የተለያዩ የመስኖ ልማቶችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሳምንቱ ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ያላትን እምቅ ሀብት ወደ ተለያዩ ልማቶች በመቀየር ተጠቃሚ በምትሆንበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በውሃና ኢነርጂ መስኮች እየተተገበረ ባለው ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ሌሎች መርሃ ግብሮች ላይም የባለድርሻ አካላትን ሙያዊ ሀሳብ ለመሰብሰብ ሳምንቱ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራልም ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ባሉ ተግዳሮቶችና መልካም እድሎች እንዲሁም በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ባላት ተጠቃሚነት ዙሪያም ምክክር ይደረጋል።

https://fanabc.com/2019/06/የኢትዮጵያ-የውሃና-የኢነርጂ-ሳምንት-በአ/


Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close