የትምህርት ሚኒስቴር ለ5ኛ ዓመት የትምህርት የእቅድ አፈጻጸም እየተዘጋጀ ባለው አዲስ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የትምህርት ልማት አጋሮች እንዲሁም ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በውይይት መድረኩ በትምህርቱ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን እና በዝግጅት ላይ ስለሚገኘው ፍኖተ ካርታ ገለፃ አድርገዋል።
በዚህም የትምህርት አስተዳደር እና አወቃቀሩን ማሻሻል፣ የመምህራንን ጥራት ማስጠበቅ፣ እንዲሁም በየደረጃው ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ማቅረብ አዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን አንስተዋል።
ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል።
