
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ100ኛ ችግኛቸውን ተክለዋል
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከተከናወነው የፅዳት ዘመቻ በተጨማሪ የችግኝ ተከላ ተከናውል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም 4 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ከተጀመረ ጀምሮ 100ኛ ችግኛቸውን ዛሬ ተክለዋል።
በፅዳትና ችግኝ ተከላ ስነ ስርዓቱ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን እና የሆስፒታሉ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።
በመላው ሀገሪቱ በየውሩ የፅዳት ዘመቻ በመከናወን ላይ ሲሆን፥ በዚህ ክረምት 4 ቢሊየን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብርም በመከናወን ላይ ይገኛል።
ዛሬም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የተከናወነው መርሃ ግብር የዚህ አካል ነው።
